ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ምዕራባዊያን ሚዲያዎች በህዝብ በተመረጠው መንግሥትና ኢትዮጵያ ላይ ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨታቸው ህዝቡን እንደመናቅ እንደሚቆጠር ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ ገለጸች።
ጋዜጠኛዋ ዘ ሬይ ዞን ከተባለ የዜና ድረ-ገጽ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ እንዳስረዳችው ከእነዚህ ተቋማት የፕሮፖጋንዳ ድጋፍ የሚያገኘው አሸባሪው የሕወሓት ቡድንም ለኢትዮጵያ ቀርቶ ላለፉት በርካታ ዓመታት ላስተዳደረው የትግራይ ህዝብም እንደማይጠቅም በተግባር አሳይቷል።
የተወሰኑ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃን በህዝብ በተመረጠው መንግሥትና ኢትዮጵያ ላይ ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨታቸው ህዝብን እንደመናቅ የሚቆጠር ድርጊት እየፈጸሙ ናቸው። የሕወሓት ሽብር ቡድን “አዲስ አበባን ለመቆጣጠር እየተቃረበ ነው” የሚለው የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙሃን የተለመደ በሐሰተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ዘገባ እና ፕሮፓጋንዳ መሆኑንም አመልክታ፤ የህዝብ ይሁንታን አግኝቶ በህግ የተመረጠን መንግሥት በሐሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ የመንግሥትና የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም የሚጎዱ ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት ለህዝብ ክብር አለመስጠት ነው ብላለች።