ከመቅደላ የተዘረፉ 13 የኢትዮጵያ ቅርሶች ከለንደን አዲስ አበባ ገቡ

ከመቅደላ የተዘረፉ 13 የኢትዮጵያ ቅርሶች ከለንደን አዲስ አበባ ገቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበመቅደላ ጦርነት ጊዜ በጀኔራል ናፒዬር ወታደሮች የተዘረፉ 13 የኢትዮጵያ ጥንታዊ የታሪክ አሻራ ማሳያ የሆኑ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

በኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ኮሚቴ፣ በእንግሊዝ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሼሄራ ዛድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባባር ባደረጉት ጥረት ባለፈው ዓመት ጳጉሜን 3 ቀን 2013 ዓ.ም በለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መመለሳቸው ይታወሳል።

የርክክብ ስነ ስርዓቱ የቱሪዝም ሚኒስትር አምሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ በኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ኮሚቴዎች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ እና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት ነው የተደረገው።

ከተመለሱትቅርሶች መካከል በነሀስ የተለበጠ ጋሻ፣ በቆዳ የተደጎሰ በእጅ የተፃፈ ጥንታዊ የብራና የፀሎት መፅሀፍ እስከነመያዣቸው፣ በመጠን ተለቅ ያለ የብር መስቀል፣ አነስተኛ መጠን ያለው የብር መስቀል፣ ፅዋ ይወሰድበት የነበረ ዋንጫ እና ማንኪያ፣ የጳጳሳት እና የካህናት አክሊል፣ የአንገት ጌጥ (ሃብል)፣ ክታብ እና የገበታ ስዕል ይገኙበታል፡፡

LEAVE A REPLY