ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሚድያ ኤክስፖን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደምታስተናግድ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሚድያ ኤክስፖን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደምታስተናግድ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደውን ዓለም አቀፍ የሚድያ ኤክስፖ ለማዘጋጀት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ኦን ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማ በትናንትናው እለት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን የማሳደግ ዓላማን አንግበው ከሚዘጋጁ መድረኮች አንዱ የሆነውን የሚድያ ኤክስፖ ኢትዮጵያ ማስተናገዷና መሳተፏ ለዘርፉ ትልቅ እምርታ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገልጿል።

የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር መገናኛ ብዙኃን በቴክኖሎጂ እና በእውቀት ሽግግር እንዲጣመሩ ማድረግ መሆኑን ኢትዮጵያ ነገ ከባለስልጣኑ ማህበራዊ ሚድያ ትስስር ገጽ ተመልክታለች።

በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው መድረክ ላይ ከ80 የሚበልጡ የመገናኛ ብዙኃን አካላት እና ከ500 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተው የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ።

ኤክስፖው ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ ኦን ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማ እና ቤዚክ ሊድ የተሰኘ ተቋም በጋራ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

በቀጣዩ ታህሳስ ወር በአህጉር አቀፍ ደረጃ ሩዋንዳ በምታስተናግደው ዲስኮፕ አፍሪካ የሚዲያ ኤክስፖ ላይ ኢትዮጵያ ተሳታፊ እንደምትሆንም ተመላክቷል።

LEAVE A REPLY