በቦረና ዞን የሞቱ እንስሳት ቁጥር 70 ሺህ ተሻግሯል

በቦረና ዞን የሞቱ እንስሳት ቁጥር 70 ሺህ ተሻግሯል

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ አስታወቁ።

ድርቁ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አመልክተዋል።

ዶ/ር ቃሲም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፥ ” 70,185 ከብቶች ሞተዋል፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት የማይችሉ በሰው ድጋፍ የሚነሱ ናቸው” ብለዋል።

ጉዳት ከፍተኛ ነው ያሉት ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ፥ ” 50,552 አባወራዎች ናቸው ከብቶቻቸውን በጉልበታቸው እያነሱ የሚገኙት ፤ ከብቶች የሞቱባቸው 28,238 አባወራዎች ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ድርቁ እንስሳት ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ በማህበራዊ ህይወት ላይ ተፅእኖ እያሳረፈ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY