የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የህወሓትን የሽብር ሴራ ማክሸፉን አስታወቀ

የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የህወሓትን የሽብር ሴራ ማክሸፉን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዘካርዬ አብዲ ካሊፍ እንደገለፁት የቀድሞ የክልሉ ልዩ ሀይል አዛዥ የነበሩት አቶ አብዱራህማን ላበ-ጎሌንና ሌሎች ግብራበሮቹ ያደረጉት የጥፋት ሙከራ ማክሸፉን ተናግረዋል።

በተንቀሳቃሽ ስልክ በመልክት መረጃ ከተለዋወጡት ሀይሎች እንደተደረሰባቸው በመግለፅ ከዚ ከአሸባሪው የህወሃት የጥፋት ሀይሎች የክልሉን ህዝብ ለማሸበር ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ተደርሶበታል ብለዋል።

ኮሎኔል ዘከሪያ አክለውም እነኚህ የጥፋት ሀይሎች አሁንም ህዝቡን ለማዋከብና በክልሉ የተጀመረውን የሰላም ጉዞ ለማሰናከል ሲሰሩ እንደነበር ተገልጿል።
ሰላም ወዳዱን ህዝብ እንደ ድሮ በሞግዝትነት ለማስተዳደር ጁንታው ወደ ስልጣን ሊመጣ ነው እንኳን ደህና መጣችሁ በሉት፣ ተነሱ የሚልና መሰል መልክቶችን እየላኩ እንደነበር ገልፀዋል።
እንደ ም/አዛዡ ገለፃ የሽብር ቡድኑንና የግብረ አበሮቹን እንቅስቃሴ በንቃት እየተከታተልን ነው ብለው፣ በዚህ ተግባር ላይ በሚሰማሩና ተባባሪዎች ላይ ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን ነው ያሉት።

LEAVE A REPLY