ሕወሓት “ሁመራ ማሳከር” የሚል ሀሰተኛ ዘመቻ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተደርሶበታል

ሕወሓት “ሁመራ ማሳከር” የሚል ሀሰተኛ ዘመቻ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተደርሶበታል

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየአሸባሪው ሕወሓት አክቲቪስቶችና ደጋፊ የምዕራባዊያን ሚዲያዎች “ሁመራ ማሳከር” የሚል ሀሰተኛ ዘመቻ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተደርሶበታል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ትናንት ኬንያዊው የደህንነት ጉዳዮች ተንታኝ የኢትዮጵያን እውነት በማዛባትና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት የሚታወቁት ሚዲያዎች በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት መሰባሰባቸውን አጋልጦ ነበር።
የኢፕድ ምንጮች የአሸባሪው የጥቅም ተጋሪዎችና ተከፋይ አክቲቪስቶች በሁመራ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል በሚል ዘመቻ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

ይህ የአሸባሪው የዲጂታል ክንፍ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ የሀሰት ዘመቻ በመክፈት መንግስትን ለመወንጀል ዝግጅት ማጠናቀቁን መረጃው የደረሰው መንግሥት አስቀድሞ በአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ላይ ማስጠንቀቂያ አውጥቶ እንደነበር የሚታወስ ነው። አስቀድሞ የተጋለጠው የጁንታው አክቲቪስትና እነሲኤንኤን ያሰቡትን ሳያሳኩ ቀርተዋል።

በወቅቱ በመስከረም ወር ላይ የCNN ዘጋቢዋ ኒማ ተመሳሳይ የሀሰት ዘገባ መስራቷና በምንጭነትም የአሸባሪው ሕወሓት አመራር የሆኑትን እና ገሬ የተባለውን ሰው እንዲሁም የቡድኑን አባላትና በማይካድራ ጭፍጨፋ የሚፈለጉ ነፍሰ ገዳዮችን በምንጭነት መጠቀሟ በስፋት በማህበራዊ ሚዲያ መጋለጡ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY