አሜሪካዊቷ ሴናተር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን ነኝ አሉ

አሜሪካዊቷ ሴናተር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን ነኝ አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአሜሪካ ምክር ቤት አባል የሆኑት ሴናተር ሼላ ጃክሰን ይህን ያሉት ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በአሜሪካ ሂውስተን ቴክሳስ ባካሄዱት የ #NOMore (በቃ) ንቅናቄ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ሴናተር ሼላ ጃክሰን በንግግራቸው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከተመረጠው የኢትዮጵያ መንግሥት እና ከኢትዮጵያዊያን ጎን እቆማለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል።

አሸባሪው ሕወሓት አገር ለማፍረስ በግልጽ ተናግሮ ወረራ እየፈጸመ መሆኑ እየታወቀ በአሜሪካን መንግሥት ሳይቀር ድጋፍ መደረጉ አግባብነት የለውም የሚለውን የሰልፈኞቹን የተቃውሞ ድምጽ በአሜሪካን ምክር ቤት እንደሚያሰሙ ሴናተሯ ለሰልፈኞቹ አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ የጥቁር አፍሪካዊያን የባሕል ማዕከል መሆኗን ሊታወቅ እንደሚገባ የጠቀሱት ሴናተሯ፤ የአድዋ ድል ለአፍሪካዊያን ምን ማለት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

LEAVE A REPLY