ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በጠቅላይ ሚኒስትሩ “ግንባር ላይ እንገናኝ” ጥሪ መሰረት የቀድሞው የህወሓት ታጋይ አቶ ሊላይ ሀይለማርያም አሸባሪው ህወሓት የጀመረውን አገር የማፍረስ ሴራ ለመመከት ወደ ግንባር ሊዘምቱ ወስነዋል።
አቶ ሊላይ እንዳስታወቁት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግንባር ቀደም ሆነው ወደ ግንባር ሲሄዱ እርሳቸው ተቀምጠው ሊመለከቱ እንደማይችሉ ገልጸዋል።
በመሆኑም አቶ ሊላይ፤ “ለአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ሰንደቃላማችን ክብር ህይወቴን እሰጣለሁ” ብለው ለዘመቻው ወስነው ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አቶ ሊላይ ከጥቅምት 4 ቀን 1968 እስከ ጥቅምት 24 1984 ዓም የህወሓት ታጋይ እንደነበሩና ይታወቃል።
በተመሳሳይ በዛሬው እለት አቶ ነአምን ዘለቀ፣ የአብኑ አመራር አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰናቸውን ይታወቃል።
ጥሪውን ተከትሎ በርካታ ታዋቂ ሰዎች ምላሻቸውን እየሰጡ ሰሆን ኀይሌ ገብረሥላሴንና ጀነራል ካሳዬ ጨመዳን ጨምሮ ድምጻዊ መሰፍን በቀለ አርቲስት ተዎድሮስ ተሾመ በማናቸውም መልክ ሀገራቸውን ለመታደግ ዝግጁ መሆናቸወን አሣውቀዋል።