ኢትዮጵያ 4 የአየርላንድ ዲፕሎማቶችን አባረረች

ኢትዮጵያ 4 የአየርላንድ ዲፕሎማቶችን አባረረች

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ የሚሰሩ 4 ዲፕሎማቶች በአንድ ሳምንት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የኢትዮጵያ መንግስት ለኤምባሲው ማሣወቁ ተሠማ።

የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትእዛዝ ማስተላለፉን ያረጋገጠ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ግን ምንም አይነት ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጠም።

በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደርን ጨምሮ 2 ዲፕሎማቶች ብቻ እንዲቀሩም ተገልጾላቸው እንደነበር የአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ውሳኔም አየርላንድ በመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በያዘችው አቋም መሆኑም ለኤምባሲው ተገልጿል ተብሏል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የአየርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሞን ኮቭኔይ ባወጡት መግለጫ፤ ዉሳኔው አስቆጭቶናል ያሉ ሲሆን አየርላንድ ለኢትዮጵያ በምታደርጋቸው ድጋፎች ታማኝነቷን ለማሳየት ጥራለች ብለዋል።

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር በአፍሪካ ማእቀፍ እንዲፈታ አየርላንድ በጽኑ ትደግፋለች ያሉት ሚኒስትሩ ውሳኔዉ ጊዜያዊ እንደሚሆን ተስፋ አለን ብለዋል።

LEAVE A REPLY