በመዲናዋ ብጥብጥ ይፈጠራል በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ ነው ሲሉ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ...

በመዲናዋ ብጥብጥ ይፈጠራል በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ ነው ሲሉ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ገልፀዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ አንዳንድ ኤምባሲዎችና የሚዲያ ተቋማት ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር ቢሞክሩም ህይወት በተለመደው መልኩ ቀጥሏል ሲሉ የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ገለጹ።

ዶ/ር ጌዲዮን ከፍራንስ 24 ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በግንባር ተገኝተው ሰራዊቱን በመምራት ላይ መሆናቸውን አስታውሰዋል። አሸባሪው ህወሓት እያደረሰው ያለውን የዜጎች መፈናቀል የንጹሃን ግድያ፣ የንብረት ዝርፊያና ውድመት ለማስቆም እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል።

አዲስ አበባ ያሉ የአንዳንድ አገራት ኤምባሲዎችና የምዕራባውያን ሚዲያዎች ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር እንደሚያወሩት ሳይሆን÷ ህይወት በተለመደው መልኩ እየቀጠለ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ከፍ ያለ ብጥብጥ ይፈጠራል በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ መሆኑን ለማረጋጋጥ ባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሱቆችና የገበያ ማዕከሎችን ሁኔታ ተዘዋውሮ መመልከት እንደሚቻልም ጠቁመዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በህግ ቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች ምርመራ ተደርጎባቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እየተሰራ መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ጌዲዮን÷ ሰዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በተጠረጠሩበት ወንጀል እንጂ የሚሰሩበትን ተቋም መሰረት አድርጎ …
[7:49 a.m., 2021-11-25] Samuel Eth: በአትላስ ሆቴል ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በሚገኘው አትላስ ሆቴል ውስጥ ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የኢዜአ ምንጮች እንዳመለከቱት ተጠርጣሪው ከሽብርተኛው ሸኔ ጋር በህቡዕ በመገናኘት ተልዕኮዎችን ሲያስተባብር ነበር፡፡

ተጠርጣሪው ባረፈበት ሆቴል ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አደንዛዥ ዕፅ፣ ሶስት ኮምፒዩተሮች፣ ሁለት ፕሪንተሮች፣ ሰባት የተለያዩ ማህተሞች፣ አንድ ላፕቶፕ እና አንድ ትልቅ ማይክ ተገኝቷል።

እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች ለመልቀቅ ያዘጋጀቸው የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ሰነዶች ከሁለት ግብረአበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመልክተዋል።

አዲስ አበባ ያሉ የአንዳንድ አገራት ኤምባሲዎችና የምዕራባውያን ሚዲያዎች ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር እንደሚያወሩት ሳይሆን÷ ህይወት በተለመደው መልኩ እየቀጠለ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ከፍ ያለ ብጥብጥ ይፈጠራል በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ መሆኑን ለማረጋጋጥ ባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሱቆችና የገበያ ማዕከሎችን ሁኔታ ተዘዋውሮ መመልከት እንደሚቻልም ጠቁመዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በህግ ቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች ምርመራ ተደርጎባቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እየተሰራ መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ጌዲዮን÷ ሰዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በተጠረጠሩበት ወንጀል እንጂ የሚሰሩበትን ተቋም መሰረት አድርጎ አለመሆኑን አስረድተዋል።

ዶክተር ጌዲዮን አለማቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪ ቡድኑ እያደረሰ ያለውን ጥፋት ከማውገዝ ይልቅ ዝምታን እንደመረጠ ገልጸው÷ የምስራቅ አፍሪካ ህብረት ልዩ መልእክተኛ ሆነው ለመጡት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የሰላም ጥረት የኢትዮጵያ መንግስት በጎ አመለካከት እንዳለውም አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY