ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦችን ለማስፈታት የሞከሩ የየፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በቁጥጥር...

ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦችን ለማስፈታት የሞከሩ የየፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በደብረ ብርሃን ከተማ ከህወሃት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ግለሰቦች እንዲፈቱ በማድረግ የተጠረጠሩት የከተማው የፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደብረ ብርሃን ሰላም እና ደህንነት ፅህፈት ቤት አሳወቀ።

ኮማንደሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህወሃት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፈቃድ ውጪ ከማቆያ እንዲወጡ አድርገዋል በሚል መሆኑን የከተማውን ኃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴን ገልጸዋል ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በዚህ ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች አመራሮች መኖራቸውን በተመለከተ ከህዝብ ጥቆማዎች እየደረሳቸው እንደሚገኝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አቶ ዳንኤል ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY