ጦርነቱ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ማድረጉ ተገለፀ

ጦርነቱ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ማድረጉ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህወሃት ኃይል በፈጸመው ወረራ ምክንያት ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዲሆኑ መዳረጋቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገለፁ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ከወር በፊት በነበረው መረጃ ከአንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ ከ1ሺህ 600 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና 300 ያህሉ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን በማስታወቅ እንዲሁም በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ የወልዲያ ዩኒቨርስቲ ስራ ማቆማቸውን በማውሳት በእነዚህ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችንና መምህራንን ወደሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የመመደብ ስራ እንደተሰራ ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም የትምህርት ሚኒስቴር በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ እየሰራ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ የትምህርት ስርዓት ላይ በማተኮር መስራት እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል፡፡

LEAVE A REPLY