የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ከአምስት አገራት የማዕድን ኩባንያዎች አመራሮች ጋር ተወያዩ

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ከአምስት አገራት የማዕድን ኩባንያዎች አመራሮች ጋር ተወያዩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ከስዊድን ካናዳ አውስትራሊያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የጣሊያን የማዕድን ኩባንያዎች ጋር ውይይቶች ማድረጋቸውን ገለጹ፡፡

ኩባኒያዎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሏቸውን ኢንቨስትመንቶች ከማሳደግ አልፈው ተጨማሪ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያገኙ ከስምምነት መደረሱንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

ውይይታችን የሀገራችን የማዕድን ዘርፍ ግዙፍ ኢቨስትመንቶችን የመሳብ አቅም እንዳለው ያረጋገጠልን ተጨማሪ ማስረጃ ነው ሲሉም በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ከአሉባልታዎች በላይ ኢትዮጵያ ዛሬም ግዙፍ ኢንቨትመንቶች አይን ማረፊያ ናት ሲሉም አክለዋል፡፡

LEAVE A REPLY