“Somoza may be a son of a bitch, but he’s our son of a bitch.” ያሉት የአሜሪካው 32ኛ ፕሬዝዳንት (1949 to 1955) ፍራንክሊን ሩዝቬልት ነበሩ፡፤ ፍራንክሊን ይህን የተናገሩት አገራቸው አሜሪካ በግዜው(1950-1956) የኒካራጓዋ አምባገነን መሪ ለነበረው ፕ/ት ሳሞዛ የምታደርገውን ድጋፍ በተመለከተ ምላሽ ሲሰጡ ነው፡፤ የሶሞዛን ገዳይነት እናውቃለን ቢሆንም ታዛዣችን በመሆኑ እንደግፈዋለን ማለታቸው ነው።
በግዜው የአሜሪካን ወዳጅነት ለማግኘት መስፈርቱ ጸረ-ኮሚኒዚም ” መሆን ብቻ ነበር። ሶሞዛም ይህን መስፈርት ያሟላ ስለነበር አምባገነን መሆኑ የአሜሪካንን ድጋፍ አላሳጣውም። ይሄው በፕ/ት ሩዝቬልት የተነገረው ታሪካዊ አባባል የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ መሰረት ሆኖ እስካሁን እንደ ቀጠለ ነው። በየወቅቱ የሚለዋወጠው የውሻ ልጅ መምረጫ መስፈርታቸው ብቻ ነው።
በ1980ዎቹ መጨረሻ የጎርቫቾቭና የሬገንን ያልተቀደሰ ወዳጅነት ተከትሎ ቀዝቃዘው ጦርነት በአሜሪካ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ። ጸረ-ኮሚኒዝም መሆን የአሜሪካንን ወዳጅነት ማግኛ መስፈርት መሆኑም በዛው አበቃ፡፤
ሩሲያን በትኖ፤ ጀርመንን ደግሞ ቀላቅሎ የተቋጨው ቀዝቃዛው ጦርነት፤ እግረ መንገዱን አሜሪካን ብቸኛዋ ለዕለ ሃያል ሃገር አደረጋት፡፤ እስከ ሚላኒየሙ መግቢያ አሜሪካ በግልጽ የወጣ አለም አቀፍ ጠላትም ሆነ የወዳጅነት መስፈርት አልነበራትም።
በሚሊያነሙ መግቢያ ላይ ግን አክራሪ-እስልምና ቡድን የአሜሪካ ጠላት ሆኖ ብቅ አለ! በተለይ ከሴፕተምበር 1/2001 ጥቃት በኋላ አሜሪካ አክራሪ እስልምናን በሽብርተኝነት ፈርጃ አለም አቀፍ ጦርነት አወጀች ! ይህ ማለት ደግሞ ጸረ – ሽብርተኝነት የአሜሪካንን ወዳጅነት ማግኛው(ውሻ መምረጫው) አዲሱ መስፈርት ሆነ ማለት ነው!
እንደ ኒካራጓዋ ፕ/ት ሶሞዛ ሁሉ በርካታ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ጸረ-ሽብር አቋም በመያዝ የአሜሪካንን ወዳጅነት አገኙ! የኛው ጉድ መለስ ዜናዊም እድሉን በመጠቀም የወቅቱ “የአሜሪካን የውሻ ልጅ ” ሆነ። የአሜሪካ ድጋፍ ሳይለየው ገደለ ፤ አስገደለ ፤ ዘረፈ አዘረፈ . . . . .. በኋላም ወደ ማይቀረበት ሄደ።
ከቅርብ አመታት በፊት ደግሞ ሽብርተኝነት የአሜሪካ ስጋት መሆኑ አበቃ። ይህ ማለት ደግሞ የአሜሪካ የውሻ ልጅ የመሆኛ መስፈርትም ይለወጣል ማለት ነው። ጥያቄው አዲሱ የአሜሪካን ወዳጅነት ማግኛ መስፈርት ምንድነው የሚል ይሆናል ? ለግዜው እኔ በግልጽ አላወቅኩትም ! ነገር ግን መስፈርቱ ምንም ይሁን ምን፤ ኢትዮጵያ አላሟላችውም! ምክንያቱ ደግሞ ጠ/ሚ አቢይ “እንቢኝ የናተ የውሻ ልጅ አልሆንም!” ማለታቸው ነው!! ተደፈርኩ ያለቺው አሜሪካም የቀድሞ የውሻ ልጆቿን ጃስ ማለቷን ቀጥላለች…….. በጠ/ሚሩ እንቢኝታ የተደሰተው 110 ሚሊዮን ህዝብ አበጀህ ብሎ ከቧቸዋል!
ታዛዥነት በቃ! ብሎ ተከትሏቸዋል!
#NoMore
ድል ለኢትዮጵያና ለህዝቧ!!