የላሊበላና ደብረሲና ከተሞች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ መንግስት አሰታወቀ

የላሊበላና ደብረሲና ከተሞች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ መንግስት አሰታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ ” የጋሸናን ግንባር ምሽጎችን በመሰባበር የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጥረዋል ” ብሏል።

በአሁን ሰዓት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ፣ ሚሊሻ እና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ ነው ሲልም አሳውቋል።

በተያያዘ ዜና በደብረሲ መንገድ ጣርማበር በመባል የሚታወቀው ቦታ ላይ በተደረገ ውጊያ የህወሃት ታጣቂዎች መደምሰሳቸውንና ደብረሲና ከተማን ሙሉ በሙሉ ከት ህነግ ሃይል ነጻ መውጣቷን መንግስት ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY