በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ነገ መከላከያን ደግፈው ሰልፍ ሊወጡ ነው

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ነገ መከላከያን ደግፈው ሰልፍ ሊወጡ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በነገው ዕለት ለአገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡

በነገው ዕለት የሚካሄደውን ሰልፍ በተመለከተ የክልሉ ተወላጅ የሆኑ የአገር ሽማግሌዎች ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ሽብርተኛው ሕወሓት ለሀገር እና ለሕዝብ ጠንቅ የሆነ የወንበዴ ስብስብ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን እታገልልሃለው በሚለው በትግራይ ሕዝብ ስም ላለፉት ዓመታት ሲነግድ፣ ሲያስርና ሲያሳድድ፣ በድህነት እንዲማቅቅ ማድረጉ ተመላክቷል።

አሸባሪው ሕወሓት የትግራይን ወጣት የሚያስጨርስ አሸባሪ ቡድን እንደሆነና የትግራይ ሕዝብን እንደማይወክል መግለጫውን የሰጡት የአገር ሽማግሌ ምዑዝ ገብረመድህን ገልፀዋል።

በነገውም ዕለት ለመንግስትና ለአገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ እንዲሁም ሽብርተኛውን ሕወሓት የሚያወግዝ ሰልፍ ከጠዋቱ 12 ጀምሮ በአበበ ቢቅላ ስታዲየም እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ የሚኖር ሁሉም የትግራይ ሕዝብ በነገው ሰልፍ ላይ ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪ አቅርበዋል።

ወጣቱ ከመንግስት ጎን በመቆም የትግራይ እናት ሀዘን ይበቃ ዘንድ ሁሉም ለሰላም እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል።

LEAVE A REPLY