ከሚሴ ጨምሮ በርካታ ከተሞች ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ ወጥተዋል ተባለ

ከሚሴ ጨምሮ በርካታ ከተሞች ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ ወጥተዋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ከሚሴ ጨምሮ በርካታ ከተሞች ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ መወጣታቸው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በ “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” ባካሄደው ኦፐሬሽን ተጨማሪ ከተሞችን ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ አውጥቷል ፤ በጥልቀት በመግባትም የአሸባሪውን ጀሌዎች የመማረክና የመደምሰስ ተግባሩን ቀጥሏል ሲል አሳውቋል።

በዚህ መሠረት በጋሸና ግንባር ቀውዝባና ጭላ ከተሞችና አካባቢያቸው ነጻ ወጥተዋል።

በወረኢሉ ግንባር በተደረገው ኦፐሬሽን አጅባር፣ ተንታ እና ዶባ ከተሞችና አካባቢያቸው ነጻ ወጥተዋል።

በከሚሴ ግንባር ማጀቴን ጭረቲን ፣ከሚሴን ፣ ርቄን ወለዲን፣ አልቡኮ ከተሞችን እና የቃሉ ወረዳን አብዛኛውን ክፍል በመቆጣጠር፣ ጥምር ጦሩ ወደ ኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ እየገሰገሰ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዛሬ እና ትናንት በተደረጉት ከፍተኛ የማጥቃት ኦፐሬሽኖች አብዛኛው የአሸባሪው ኃይል ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲበተን ተደርጓል ” ያለ ሲሆን አስቀድሞ ነጻ በወጡት በምሥራቅ፣ በምዕራብና በመሐል ግንባር በሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች መንግሥታዊ አስተዳደር ተመልሶ በመደራጀት ሥራውን ጀምሯል ብሏል።

LEAVE A REPLY