ጄፍ ፒርስና (ፕ/ር) አን ፊትዝ ጌራልድ የእውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው

ጄፍ ፒርስና (ፕ/ር) አን ፊትዝ ጌራልድ የእውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው

ካናዳውያኑ ፕ/ር ጄፍ ፒርስና አን ፊትዝ-ጌራልድር ለኢትዮጵያ እውነት ወግነው በመሞገት እያከናወኑት ላለው ሥራ የእውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው።

የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ (ኢክናስ) የቶሮንቶ ቻፕተር አሸባሪው ሕወሓት በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ትናንት ማምሻውን ተካሄዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ኢክናስ ለካናዳውያኑ ጄፍ ፒርስና አን ፊትዝ-ጌራልድ (ፕ/ር) ከኢትዮጵያ እና ከእውነትጎን ቆመው ስለሚያደርጉት ሙግት ከክሪስታል ማዕድን የተቀረጸ የእውቅና ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

ካናዳውያኑ ለተሰጣቸው እውቅና ምስጋናቸውን አቅርበው፤ አሁንም ሆነ ወደ ፊትም የኢትዮጵያን እውነታ ማስረዳትና መሟገታቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ጋዜጠኛ፣ የታሪክ ምሁርና ደራሲው ጄፍ ፒርስ ምዕራባውያን አገራትና አሸባሪዉ ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ የወጠኗቸዉን ሴራዎችና የሐሰት መረጃዎችን በማጋለጥ ይታወቃል።

በቅርቡ በዋሺንግተን ዲሲ የአንዳንድ ምዕራባዊያን አገራት ዲፕሎማቶች ከአሸባሪው ሕወሓት አመራር ጋር ለአሸባሪው ቡድን ድጋፍ ማድረግና የሽግግር መንግሥት ማቋቋም በሚል ያደረጉትን የቪዲዮ ውይይት ይፋ በማድረግም ማጋለጡንም የታወሳል።

LEAVE A REPLY