የአዲስ አበባ ካቢኔየ500 ሚልየን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ እንዲቀርብ ዉሳኔ አሳለፈ

የአዲስ አበባ ካቢኔየ500 ሚልየን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ እንዲቀርብ ዉሳኔ አሳለፈ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የከተማ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ተዘዋዋሪ ፈንድ እንዲቀርብ ዉሳኔ አሳልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ለሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት የግብርና ምርቶች የሚያቀርቡበት ብድር ማቅረብ አስፈላጊ በመሆኑ ለጤፍ እና ለስንዴ ግዢ የሚውል 500 ሚልየን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ እንዲቀርብ ወስኗል።

በውሳኔው መሰረት የግዢ ሂደቱም የሸማቾች ሕብረት ስራ ማኀበራት ግዢውን በቀጥታ ከአምራች መሰረታዊ ማኀበራት እንደሚፈጸም ከአስተዳደሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት የትስስር ገጽ ተመልክተናል፡፡

በተጨማሪም በሱማሌ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ50 ሚልየን ብር ለሱማሌ ክልል እና የ50 ሚልየን ብር ለቦረና ዞን የአይነት ድጋፍ እንዲደረግ በመወሰን ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ የካቢኔ አባላት ኮሚቴ ሰይሟል፡፡

LEAVE A REPLY