ሕወሓት በአማራ እና አፋር ክልል 49 አምራች ተቋምትን ማውደሙ ተገለፀ

ሕወሓት በአማራ እና አፋር ክልል 49 አምራች ተቋምትን ማውደሙ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአሸባሪነት የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን በወረራ ይዟቸዋል በተባሉት አካባቢዎች በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ 49 አምራች ተቋምትን አውድሟል ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ቡድኑ በኃይል በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ አምራች ተቋማትን ማውደሙን እና መዝረፉን የሚኒስቴሩ የመሰረተ ልማትና ግብአት አቅርቦት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ መግለጻቸው በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ይፋዊ የትስስር ገጽ ተመላክቷል።

በአማራ ክልል የሚገኙ 11 የግብርና ማቀነባበሪያ፣ 10 የምግብና ምግብ ነክ አምራች ተቋማትን፣ 11 የቆዳና ጨርቃጨርቅ፣ 3 የብረታብረት እንዲሁም 10 የኬሚካል አምራች ተቋማት በሕወሓት ኃይል መውደማቸዉ እና መዘረፋቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም በአፋር ክልል 4 በተለያዩ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አምራች ተቋማት መውደሙ ተገለፀ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ተቋማቱ የጉዳት መጠንን የሚለይ ግብረ ኃይል እንደሚያሰማራ የገለጸ ሲሆን ተቋማቱ ወደ ማምረት ሂደታቸው እንዲመለሱ ትኩረት ይሰጣል ብሏል።

LEAVE A REPLY