የትግራይ እናቶች ልጆቻችንን እያሉ ህወሓትን እየሞገቱ መሆኑ ተሰማ

የትግራይ እናቶች ልጆቻችንን እያሉ ህወሓትን እየሞገቱ መሆኑ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የትግራይ እናቶች ልጆቻችንን የት አደረሳችኋቸው እያሉ አሸባሪው ህወሓትን እየሞገቱ ነው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ የሽብር ቡድኑ በትግራይ እናቶች ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ተነስቶበታል ብለዋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የትግራይ እናቶች በአሸባሪው ህወሓት ስብሰባዎች ላይ አንገኝም እያሉ ነው።

ተገደው የተገኙትም ልጆቻችንን የት አደረሳችኋቸው ብለው እየሞገቱ ነው። በዚህም ምክንያት አሸባሪው ቡድን ሕዝባዊ ቁጣ ተነስቶበታል ብለዋል።

የትህነግ አመራር እርስ በእርሳቸው መናቆር አብዝተዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የአሸባሪው ቡድን ግብዓተ መሬት ሩቅ እንዳልሆነ ያሳያል ብለዋል።

ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው፤ ተላላኪው ሸኔ ላይ አስፈላጊው እርምጃ እየተወሰደ ነው፤ እርምጃውም ይቀጥላል ብለዋል።፡፡

LEAVE A REPLY