የዓለም የጤና ድርጅትና ዩኔስኮ አሸባሪው ሕወሓት ያደረሰውን ውድመት እንዲያጋልጡ ኢትዮጵያ ጠየቀች

የዓለም የጤና ድርጅትና ዩኔስኮ አሸባሪው ሕወሓት ያደረሰውን ውድመት እንዲያጋልጡ ኢትዮጵያ ጠየቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ዐአቀፍ ተቋማት ዳይሬክተር ጀነራል ዮሴፍ ካሳዬ ከዩኔስኮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሚኮ ዮኮዝኪ እና ከዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ቦሪማ ሳምቦ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ዳይሬክተር ጀነራሉ ሁለቱ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ሕወሓት መራሹ ቡድን በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የጤና ተቋማት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ቅርሶች ላይ ያደረሰውን እና እያደረሰ ያለውን ውድመት ለመግለጽ ዳተኛ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በምጣኔሃብት፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ቅርሶች ላይ የሚያደርሰው ውድመት የሚያስኮንነው ቢሆንም የዓለም ዐቀፍ ተቋማት ዝምታ ግን አሸባሪ ቡድኑ ለተጨማሪ ውድመት እና ጥፋት እንዲነሳሳ የልብ ልብ መስጠቱን አስምረውበታል፡፡

የሁለቱ ድርጅቶች ኃላፊዎች በበኩላቸው በዳይሬክተሩ ለተሰጣቸው ማብራሪያ አመስግነው በተለይ በሰዎች ደኅንነት እና ታላላቅ ቅርሶች ዙሪያ በትኩረት እንደሚሰሩ ማስረዳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ተመልክተናል።

LEAVE A REPLY