ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሕግ የማስከበር ዘመቻው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ እውነትን የካደ ጫና እያደረገ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ ከአውሮፓ ኅብረት የበላይ አካላት ጋር በማሴር በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ለማድረግ ከሰሞኑ ፊርማ ሲያሰባስብ አፍሪካዊያን አለመሳተፋቸው የተቋሙን ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል ብሏል፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ የተባበሩት መንግሥታት የሰብብዊ መብት ምክር ቤት የአፍካዊያን ችግርን በአፍሪካዊያን የመፍታትን አቅምን ለማዳከም አልሞ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
አሸባሪው ሕወሓት በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ የፈጸማቸውን የጅምላ ግድያና ሌሎች ወንጀሎች የመንግሥታቱ የሰብኣዊ መብት ምክር ቤቱ ምንም አይነት ትኩረት ሳይሰጥ ማለፉ ምክር ቤቱ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ መሆኑን ያመላክታልም ብለዋል፡፡