ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፌደራል ፖሊስ አሸባሪውን የሸኔ ቡድን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ ጋዜጠኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ጋዜጠኞቹ ኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳ ቀኝ ወረዳ የሚንቀሳቀሰውን የሽብርተኛውን ሸኔ ቡድን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከታትሎ በመቅረጽና ቃለ መጠይቅ በማድረግ መረጃዎችን በማሰባሰብ ኬንያ ለሚገኘው እና የአሶሽየትድ ፕረስ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ለሆነው ግብጻዊው ካሊድ ካዚሃ በመላክ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ነው የተናገሩት።
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት አንደኛ ተጠርጣሪ አሚር አማን የአሶሺየትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ፣ ሁለተኛ ተጠርጣሪ ቶማስ እንግዳ የካሜራ ባለሞያ እና ሦስተኛ ተጠርጣሪ አዲሱ ሙሉነህ የኤፍቢሲ ጋዜጠኛ መሆናቸው ተገልፆዋል