የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወልዲያን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወልዲያን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የወልዲያ ከተማን ጨምሮ የሰሜን ወሎ ዞን ሙሉ ለሙሉ ከአሸባሪው ቡድን ነፃ መውጣቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ኃይል ዘመቻ ለኀብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መርህ በተቀናጀ መንገድ ማጥቃት ከጀመረበት ቀን አንስቶ አከርካሪው የተመታው ጠላት የማድረግ አቅሙ፣ ፍላጎቱ እና ስነልቦናው ብትንትኑ መውጣቱን ነው መንግስት ያስታወቀው።

ትላንት ሌሊቱን በሙሉ እና ዛሬ ረፋዱን ጀግኖቹ የወገን ጥምር ኃይሎች ከአየር ኃይል ጋር ባደረጉት የተቀናጀ የማጥቃት ዘመቻ የሳንቃ፣ የሲሪንቃ፣ የሰሜን ወሎ ዋና ከተማ የሆነችው ወልዲያን፣ ሃራን፣ ጎብዬን፣ ሮቢት እና ቆቦን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል ብሏል መግለጫው።

የወገን ጦር በተያዙት አካባቢዎች የመጨረሻ ሙከራ ሲያደርግ የነበረውን የጠላት ጦር ደምስሶታል።

ከድምሰሳ ተርፎ እየፈረጠጠ ያለውን የጠላት ኃይል የወገን ጦር እግር በእግር እየተከታተለ ሙት፣ ቁስለኛ እና ምርኮኛ እያደረገው እንደሚገኝም ተገልጿል።

የአካባቢው ሕብረተሰብ በተለይም ወጣቶች ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት በየጥሻው እየተሽሎከለከ ለማምለጥ የሞከረውን የጠላት ጀሌ በመልቀም ምንም አይነት ንብረት፣ ተተኳሽ እና እራሱንም ይዞ እንዳይወጣ የላቀ የጀግንነት ጀብድ መፈፀሙም ነው የተገለፀው።

LEAVE A REPLY