20 የአሸባሪ ሸኔ አባላት በምስራቅ ወለጋ ዞን በቁጥጥር ስር ዋሉ

20 የአሸባሪ ሸኔ አባላት በምስራቅ ወለጋ ዞን በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶ ጊዳ ወረዳ 20 የሸኔ ሽብር ቡድን አባላት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የጉቶ ጊዳ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ሳጂን ከተማ ኦልጂራ እንደገለጹት በቁጥጥር ስር ከዋሉት 20 የአሸባሪው ሸኔ አባላት መካከል 7ቱ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል በሰላም እጃቸውን የሰጡ ናቸው፡፡

ከሽብር ቡድኑ አባላት በተጨማሪም 16 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ፣ 11 ኋላ ቀር የጦር መሳሪያ እና ጥይቶች መያዛቸውን ነው የገለጹት፡፡
ከዚህ ባለፈም ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ የተለያዩ አልባሳት እና ብሮች መያዛቸውን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

LEAVE A REPLY