የአሸባሪውን ግፎችና የወደሙ ንብረቶች በመርማሪ ቡድን እየተጣራ ነው 

የአሸባሪውን ግፎችና የወደሙ ንብረቶች በመርማሪ ቡድን እየተጣራ ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ነጻ በወጡ አካባቢዎች የአሸባሪው ሕወሓት ግፎችና የወደሙ ንብረቶችን እንዲሁም ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ የተዋቀሩ መርማሪ ቡድኖች ምልከታ እያደረጉ መሆናቸውን መንግሥት አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በጦርነቱ የኢትዮጵያዊነትን አብሮነትና ኅብረት ለዓለም አሳይተናል ያሉ ሲሆን ከአሸባሪው ነጻ በወጡ አካባቢዎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በወንጀል የሚጠረጠሩ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ የተዋቀሩ መርማሪ ቡድኖች ምልከታ እያደረጉ እንደሆነና ዓለም ዐቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው ዓለም ዐቀፍ ህግጋትን ይከተላል ብለዋል፡፡

በተለይ በጤናው ዘርፍ የጤና ተቋማትን መልሶ በማቋቋም ረገድ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ከ35 በላይ ሆስፒታሎች፣ 418 ጤና ጣቢያዎች፣ 1ሺሕ 700 በላይ ጤና ኬላዎች በአሸባሪው ቡድን መውደሙን አመልክተዋል፡፡

ተማሪዎችን በፍጥነት ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

LEAVE A REPLY