የታሪክ ጸሐፊና ተመራማሪው ጄፍ ፒርስ አሸባሪው ትሕነግ ያደረሳቸው ውድመቶችን ተዘዋውሮ ተመለከተ

የታሪክ ጸሐፊና ተመራማሪው ጄፍ ፒርስ አሸባሪው ትሕነግ ያደረሳቸው ውድመቶችን ተዘዋውሮ ተመለከተ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የታሪክ ጸሐፊ ተመራማሪና ጋዜጠኛ ጄፍ ፒርስ አሸባሪው ትሕነግ የእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን መፈፀሙን ገለፀ።

አሸባሪው ትሕነግ በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲሰነዝር መክረሙን ያስታወቀው ጄፍ ፒርስ
በቅርቡ በዋሺንግተን ዲሲ የአንዳንድ ምዕራባዊያን አገራት ዲፕሎማቶች ከአሸባሪው ሕወሓት አመራር ጋር ለአሸባሪው ቡድን ድጋፍ ማድረግና የሽግግር መንግሥት ማቋቋም በሚል ያደረጉትን የቪዲዮ ውይይት ይፋ በማድረግም ማጋለጡንም የታወሳል።

በዚህም ጨጭሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን የትሕነግ የጥፋት ኃይሎች በተደጋጋሚ በመድፍ መመታታቸውን ገልጿል፡፡

ጉዳቱን የቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮች መልሶ ለመጠገን እንዳስቸገራቸውም ጠቁሞ
በተመሳሳይ አሸባሪው ቡድን ጭካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ድርጊቱን በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ላይ መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

በከተማዋ ለቱሪስቶች ማረፊያ የሚሆኑ ሆቴሎችና ሬስቶራንቶችን አውድሟልም ብሏል፡፡ በተጨማሪም በፖሊስ ጣቢያዎችና በከተማ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የአሸባሪው ትሕነግ የጥፋት እጅ አርፎባቸዋል ነው ያለው፡፡
የትህነግ ቡድን በደረሰባቸው ቦታዎች ንጹሃንን መግድሉንና ሴቶችና ህጻናትንም መድፈሩንም አክሎ ገልጿል፡፡

LEAVE A REPLY