ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ለጦርነቱ ተጎጂዎች መልሶ ማቋቋሚያ በገንዘብ ሚኒስቴር የቀረበለትን የ5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ማፅደቅን ጀምሮ 6 ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡
ምክር ቤቱ ገንዘብ ሚኒስቴር ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ ይጸድቅ ዘንድ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
የነዳጅ ውጤቶች መሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመከረም ሲሆን፤ ጎልተው የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የነዳጅ ግብይት ሪፎርም በአገር ደረጃ በእቅድ ተይዞ እየተከናወነ መሆኑን አንስቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ እየሰፋ የመጣውን በፖሊሲ ያልተደገፈ የነዳጅ ድጎማ ከተመረጡ ተሸከርካሪዎች በሂደት ለመቀነስና ለማስቀረት የሚያስችል የዋጋ ማስተካከያ ጥናት በማድረግ የቀረቡ የውሳኔ ሐሳቦችን ለመተግበር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተዘጋጅቶ ቀርቧል ያለም ሲሆን የውሳኔ ሐሳቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ከዛሬ ጀምሮ ከስድስት ወር የዝግጅት ምዕራፍ በኋላ ተፈፃሚ እንዲሆን ወስኗል፡፡
ላለፉት 25 ዓመታት በሥራ ላይ የነበረውን አሰራር በማሻሻል ወጥነትና ግልጽነት ያለው የአሰራር ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ የውሳኔ ሐሳቡ እንዲፀድቅ ተደርጓል
ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በድንጋይ ከሰል ማዕድን ልማት ላይ ከስምንት ድርጅቶች ጋር ለማድረግ ያሰበውን ስምምነት እንዲፈራረም ተወስኗል፡፡

























