ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሰሞኑን ጉንፋን መሰል ወረርሽኝ በርካቶች በዚህ ህመም ተይዘዋል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልም ለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ጠቃሚ መረጃን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይዞ ወጥቷል።
የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል ብርድ ብርድ ማለት የመገጣጠሚያ ህመም የጀርባ ህመም የጡንቻ ህመም ምግብ ፍላጎት መቀነስ ኃይለኛ ራስ ምታት እንዳለው የገለፀው ሆስፒታሉ የህመሞቹም ምክንያት ጨምረው ገልጸዋል
ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸዉ ለምሳሌ ኮሮና ቫይረስ ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው ብለዋል።
የመከላከያ መንገዶቹን ጠቅሰው ገልፀዋል ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን በመሸፈን የእጅ እና አካል ንክኪ በመቀነስ ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አለመገኘት ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድ/በጨርቅ በመሸፈን መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ የሉ ሲሆን ህመሙን የተሰማው ሰው
ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫ ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠልም የአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም፣ ትኩስ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
እነዚህን መፍትሄዎ እያደረጉ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል በመግለጫው።

























