ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ከሕግ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ የቀረበለትን ማብራሪያ እና የዉሳኔ ሃሳብን መሰረት አድርጎ መጽደቁን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ዙር ባደረገው የህብረተሰብ ክፍሎችን ሃሳብ የማሰባሰብ ሂደት እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት በረቂቅ አዋጁ ላይ በተካተቱ አንቀጾች ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታዉቋል።
በእዚህ ሂደት መሰረት ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ ሃሳብ የምክር ቤቱ አባላት በ13 የተቃዉሞ ድምጽ፣ በአንድ ድምጸ ተአቅቦና በአብላጫ ድምጽ ሊጸድቅ ችሏል።

























