በአፋር ክልል 759 ትምህርት ቤቶች በአሸባሪው ህወሓት መውደሙን ተገለፀ

በአፋር ክልል 759 ትምህርት ቤቶች በአሸባሪው ህወሓት መውደሙን ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሽብር ቡድኑ በክልሉ 4 ዞኖችና 21 ወረዳዎች ባደረሰው ጉዳት 694 ትምህርት ቤቶች በከፊል፣ 65 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ፣ በድምሩ 759 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል።

የወደሙትን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባትና የትምህርት ሥራውን ለማስቀጠል በክልሉ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትንና አመራሮችን ያካተተ ቡድን ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን ተገልጿል።

ለመልሶ ግንባታው የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ ተሰልቶ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የአፋር ብሔራዊ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ መሐመድ ገልጸዋል።

የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ገንብቶ የትምህርት አገልግሎትን በማስቀጠል ረገድ ህብረተሰቡ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የጭፍራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ አብዱ በበኩላቸው በተለይ አንጋፋ እና በአፈጻጸማቸው ሞዴል በሆኑ ትምህርት ቤቶች የጉዳት መጠኑ የከፋ መሆኑን ጠቅሰው ድርጊቱ ወራሪው ኃይል ለአፋር ህዝብ ያለውን የጠላትንት ጥግ ያሳየ መሆኑን መግለፃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

LEAVE A REPLY