ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቤተ መጽሐፍቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መርቀው ከፍተውታል፡፡
ኢትዮጵያ የምትገነባው በዕውቀት ማዕከላት ውስጥ ነው!” ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ የምትገነባው በዕውቀት ማዕከላት ውስጥ ነው! ዛሬ የምንመርቀው ቤተ መጻሕፍት አብርሆት ተብሎ የተሰየመ ሲሆን አብርሆት እውነትንና ዕውቀትን መሠረት በማድረግ ከድንቁርና ቀንበር ነጻ የመውጣት ሂደት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩበመግለጫቸው እንዳሉት እውነትን በአመክንዮ፣ በክርክር፣ በማስረጃ፣ በምርምር፣ የመፈለግ መንገድ ነው። ዕውቀት ወደ እውነት ለመድረስ ሁነኛው ጎዳና ነው ብሎ ያስባል። በአመክንዮ የሚመሠረት የሰው ልጆች ማኅበራዊ ኑሮ በወንድማማችነት ላይ የተመሠረተ፣ መቻቻል ያለበት፣ ነጻነትን የሚያጎላና ለለውጥ ልብን ክፍት ያደረገ እንደሆነ ያምናል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ስለ ቤተ መፅሐፍቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል የአብርሆት ቤተ መጽሐፍት በ19ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ፤ በአራት ወለሎች ተከፍሎ በውስጡ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን መፃህፍት የሚይዝ መደርደርያ የተገጠመለት እና በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ አስር ቤተ መጽሐፍት አንዱ እንደሆነም የተናገሩ ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቤተ መጽሐፍቱ ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወረቀት አልባ መፃህፍትና 300 ሺህ ጥናታዊ ፅሑፎች የያዘ መሆኑን ገልጸዋል
ቤተ መጽሐፍቱ በውስጡ ከማንበቢያ ስፍራ በተጨማሪ 8 የመፃህፍት መሸጫ ሱቆች፤ የስብሰባ አዳራሾች፤ ካፍቴሪያ እና የህጻናት ማንበቢያ ስፍራዎችን ያካተተ መሆኑንም ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም አምፊ ትያትር እና መጫዎቻ ስፍራዎች እንዲሁም ከ120 በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ መመገቢያ ካፌ፣ ስምንት የመጻህፍትና ተጓዳኝ አገልግሎት መስጫ ሱቆች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመግለጫቸው ጨምረው ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዘመን፣ መጀመሪያ ደረጃቸውን የጠበቁ ክልላዊ አብያተ መጻሕፍት እንዲኖሩን፤ በመቀጠልም ዞናዊና ወረዳዊ አብያተ መጻሕፍት እንዲኖሩን እንሠራለን ያሉ ሲሆን።
ይህ ቤተ መጻሕፍት ሲታሰብ፣ ሲገነባና ሲሟላ አስተዋጽዖ ያደረጉትን ሁሉ በዚሁ አጋጣሚ ላመሰግን እወዳለሁ። ሕዝቡ ቤተ መጻሕፍቱን ተንከባክቦ፣ እንዳይበላሽ ጠብቆ፤ ሲጎዳ ጠግኖ፤ ሲጎድል አሟልቶ ለልጅ ልጅ በሚተርፍ መንገድ እንዲጠቀምበት አደራ እላለሁ ብለዋል።

























