ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ‹‹አዲስ ቀደምት›› የቅድመ ታሪክ ስፍራ በደቡብ ኢትዮጵያ በያንዳ ቱሚ ሸለቆ ኮንሶ ዞን መገኘቱ ተገለፀ።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴማቲክ ፈንድ ከተሰኘ አጋር በተገኘ የምርምር ገንዘብ ለዓመታት በተደረገ ጥናት በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ ዞን በያልዳ ሸለቆ የእንሰሳት ቅሪተ አካል እና የጥንት ሰዎች የተገለገሉባቸው የድንጋይ መሳሪያዎች ተገኝተዋል።
ግኝቱ ከዛሬ 2 እና 3 ሚሊየን ዓመት በፊት የነበሩ የእንሰሳ ዝርያ ዓይነቶችን ማሳየት የሚችል ነው ተብሏል። በጥናቱ የጥንት የዝሆን ዝርያዎች፣ የጋማ የከብት ዝርያዎች፣ የአሳማ ዝርያዎች፣ የጉማሬ ቅሪተ አካል፣ የየብስ እና የባሕር እንሰሳት ቅሪተ አካሎች ተገኝተዋል።
ይህ ግኝት ከቅሪተ አካል እና የድንጋይ መሳሪያ ክምችት እንዲሁም ክምችቱ ከተገኘበት ውስን መልከዓምድር አንፃር በኢትዮጵያ ከተገኙ ግኝቶች በቀደምትነት ሊመደብ የሚችል ነው ተብሏል።