በአስቸኳይ አዋጁን ሽፋን የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ፖሊሶች ላይ ተከሰሱ

በአስቸኳይ አዋጁን ሽፋን የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ፖሊሶች ላይ ተከሰሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሽፋን በማድረግ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በተጠረጠሩ 7 የፖሊስ አባላት ላይ ክስ መመስረቱን ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የፖሊስ አባልነታቸውን ሽፋን በማድረግ ምርመራ የማከናወንና የግል ተበዳዮችን የመያዝ የስራ ድርሻ ሳይኖራቸው እና ምንም አይነት ትዕዛዝ ሳይሰጣቸው በወቅታዊ ጉዳይ በህግ ትፈለጋለህ ፤ ከምትታሰር ገንዘብ ስጠን ብለው የጠየቁ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ላይ ክስ መመስረቱ ታውቋል።

አራት የፌዴራል ፖሊስ አባላት 260 ሺህ ብር ተቀብለው መከፋፈላቸው እንደተደረሰበት የገለጸው ሚኒስቴሩ ፥ 70 ሺህ ብር በተቀበሉ ሶስት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ መዛግብት ክስ መስርቶ ጉዳዩም በፍርድ ቤት የክርክር ሂደት ውስጥ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የጸጥታ አካላት የተጠለባቸውን ሓላፊነት በተሟላ እና ጥብቅ በሆነ ፖሊሳዊ ስነምግባር እንዲወጡ ፤ ህብረተሰቡም እንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባራትን ሲመለከት ጥቆማውን ለጸጥታ አካላት እንዲሁም በሚኒስቴሩ ነጻ አጭር የስልክ መስመር 6044 በመደወል ሊያሳወቅ እንሚገባ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY