ጠ/ሚ አብይ እስረኛ ፍታ ያለኝ ማንም መንግስት የለም አሉ

ጠ/ሚ አብይ እስረኛ ፍታ ያለኝ ማንም መንግስት የለም አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || እስረኞቹ እንዲታሰሩም ሆነ እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀረበ “አንድም መንግስት” እንደሌለ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “አንድም መንግስት ‘እነዚህ ሰዎች ታስረዋልና ፍታ ብሎ የጠየቀኝ የለም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የእስረኞች ፍቺ ጉዳይ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ ውይይት የተደረገበት ከአንድ ወር በፊት መሆኑን የጠቆሙት አብይ፤ ውሳኔው “እስከ ታች ድረስ” ውይይት የተደረገበት እንጂ “እንግዳ ጉዳይ” እንዳልነበር ገልጸዋል።

ሁሉም ክልል ተወያይቶበታል። አሁን ድንገት ደርሶ ‘ድንገት ሆነብኝ’ የሚለው ተቀባይነት የለውም። ሲሉ ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር ዛሬ ባደረጉት ውይይት ላይ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY