አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነዉ ተባለ

አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ በመጪዉ ሳምንት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ።

ልዩ መልዕክተኛዉ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሳዑዲ አረቢያ እና ሱዳንን እንደሚጎበኙም የሚጠበቅ ሲሆን በሀገራቱ በተከሰቱ ግጭቶችን እና በአለመግባባቶች ዙሪያ ይመክራሉ ነዉ የተባለዉ ።

እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር 17_20ባሉት ለአራት ቀናት ዉስጥ በሚኖራቸዉ ጉብኝት በኢትዮጵያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የሚመክሩ ሲሆን እየተካሄደ ያለዉ የህግ ማስከር ዘመቻ መቋጫ መሆን ያለበት ጉዳይ ላይ ይመክራሉ ተብሏል ።

አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን ተክተዉ በቅርብ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኘነት በመሆን መሾማቸዉ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY