መንግስት በወይ ብላ ማሪያም አካባቢ ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂዎችን ለህግ እንደሚያቀርብ ገለፀ

መንግስት በወይ ብላ ማሪያም አካባቢ ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂዎችን ለህግ እንደሚያቀርብ ገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የጥምቀት በዓል በመላ አገሪቱ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁን የገለፀ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እና በቡራዩ አዋሳኝ ወይ ብላ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ በተፈጠረው ችግር በዓሉ መስተጓጎሉና በሰዎች ላይም ሞትና ከባድ ጉዳት መድረሱ በተመለከተም መግለጫ ሰጥቷል።

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እና በቡራዩ አዋሳኝ ወይ ብላ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ለተፈጠረው ችግርና ለጠፋው የሰው ህይወት ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለሕግ እንደሚያቀርብ ገለጸ ሲሆን መንግስት ለጉዳዩ ተጠያቂ ይሆናሉ ያላቸውን አካላት “የተለያዩ አካላት የሸረቧቸውን ሤራዎች ሕዝቡና የጸጥታ አካላት ተናብበውና ተቀናጅተው አክሽፈውታል። ከማለት በዘለለ ስለተጠርጣሪዎች የሰጠው ፍንጭ የለም።

የኢትዮጵያን ገጽታ ማበላሸት የፈለጉ አካላት የጥምቀትን በዓል በመረበሽ ተልኳቸውን ለማሳካት ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም ብሏል መግለጫው።

LEAVE A REPLY