አፄ ምኒልክ በአድዋ የተዋጉበት ጎራዴና ሌሎች ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ

አፄ ምኒልክ በአድዋ የተዋጉበት ጎራዴና ሌሎች ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት ላይ የተዋጉበት ጎራዴ ጨምሮ ከጎራዴው ጋር ተዘርፎ የነበረው የእንጨት መስቀልም እንዲሁ ተመልሷል በተጨማሪም ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተላላኳቸው ደብዳቤዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ፖስት ካርዶችና የጽሁፍ እና የምስል ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ቅርሶቹን ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስረክቧል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ወደ አገር የተመለሱትን ቅርሶች ጠብቆ የማቆየት ሀላፊነትን ተቀብለናል ብለዋል።

ቅርሶቹ በታሪክም የሚነገረውን የኢትዮጵያን ቀደምትነትና ሃያልነት በተግባር የሚያሳዩ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን በተለያየ መንገድ ለማጠልሸት ለሚጣጣሩ አካላት ምላሽ የሚሰጡም ናቸው ብለዋል።

ቅርሶቹን ጠብቆና ተንከባክቦ ከማስቀመጥ ባሻገር በቀጣይ የማስተዋወቅ ስራው እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴን ጨምሮ የማህበሩ አባላትና እንግዶች ተገኝተዋል።

LEAVE A REPLY