ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግሥት የሃይማኖትንና የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሕጋዊ ተልዕኮውን ሕግና አሰራርን መሰረት አድርጎ እንዲሰራ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ።
ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በቡራዩ ከተማ ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን የታየው ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ሊታረምና ይህንን ድርጊት የፈፀሙ አካላትንም መንግስት ተከታትሎ ተጠያቂ እንዲያደርግ ጉባኤው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
በተጨማሪም መንግሥት ለመላው ሕዝብ የተደረሰበትን ውጤት በግልጽ እንዲያሳውቅ ጉባኤው በአጽንኦት አሳስቧል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ቡድኖች የሃይማኖት ተቋማትን የጥላቻና የብጥብጥ ምክንያቶች ለማድረግ የሚደረገውን አዝማሚያ ጉባኤያችን አጥብቆ ያወግዛል ብሏል።