በቤኒሻንጉል ክልል ሁለት ዞኖች ከ2 ዓመት በላይ የመብራት አገልግሎት አላገኙም ተባለ

በቤኒሻንጉል ክልል ሁለት ዞኖች ከ2 ዓመት በላይ የመብራት አገልግሎት አላገኙም ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ዞኖች በፀጥታ ችግር ምክንያት ከ2 ዓመት በላይ ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት አላገኙም።

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መለሰ በየነ ለአሐዱ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ባለፉት ዓመታት በመተከል እና ካማሽ ዞኖች በታጣቂዎች የተስተጓጎለው የመብራት አገልግሎት መፍትሔ ሳያገኝ እስካሁን ድረስ ዘልቋል ብለዋል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርጓል በተለይም በከተሞች አካባቢ በመብራት ኃይል ብቻ ስራቸውን የሚሰሩ ዜጎችን ለስራ አጥነት ተጋላጭ አድርጓቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ችግሩ መቼ ይፈታል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በቀጣይ የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሲስተካከል እግር በግር በመከተል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመመለስ ይሰራል ሲሉ መልሰዋል።

LEAVE A REPLY