በአፋር በኩል ጦርነቱ መቀጠሉን ክልሉ አስታወቀ

በአፋር በኩል ጦርነቱ መቀጠሉን ክልሉ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በአብአላና በመጋሌ ወረዳ የከፈተውን ውጊያ አጠናክሮ መቀጠሉን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።

ቡድኑ ምንም አይነት ሰብአዊነትና ርህራሄ ፈፅሞ ሳያሳይ በንፁሀን ዜጎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመክፈት እያሸበረ ይገኛል ሲል ነው የክልሉ መንግስት ያስታወቀው።

እያደረሰ ባለው ጥቃትም የአፋር ንፁሃን ኢላማ በማድረግ የሽብር ተግባሩን በማስፋት ላይ መሆኑንም ገልጿል።

በዛሬው እለትም በኪልበቲ ረሱ (ዞን) በተለያዩ ቦታዎች የአፋር ክልልን ወሰን ጥሶ በመግባት በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በመክፈት በርካታ ንፁሀንን ለጉዳት መዳረጉንም አስታውቋል።

ይሁንና ሁሌም በማጭበርበርና በውሸት ፕሮፖጋንዳ እድሜውን የሚያራዝመው ጁንታው በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በኩል ዘልቆ በመግባት ንፁሀን የጎዳ ቢሆንም ጥቃት እንደተፈፀመበት አስመስሎ በማቅረብ አሁንም ማደናገሪያውን እየነዛ ይገኛል።” ሲልም ነው የክልሉ መንግስት ያስታወቀው።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ የህወሃት ቡድን በአራት ዞኖች ውስጥ በ 21 ወረዳዎች ወረራ በማካሄድ የአፋር ህዝብን በአሰቃቂ ሁኔታ ቢጨፈጭፍም፣ በብዙ ቢሊየኖች የሚገመት ሀብት ንብረት ቢያወድም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ እንዲሰደድ ቢያደርግም ለጎረቤት ትግራይ ህዝብ ሰብአዊነት ሲባል እርዳታ በአፋር አብአላ በኩል እንዲያልፍ እየተደረገ ነበር ብሏል።

ነገር ግን ጁንታው ለትግራይ ህዝብ እንኳን ምንም አይነት ርህራሄ እና እዝነት ባለመኖሩ በዚሁ ቀጠና ግጭት በመፍጠር አካባቢው የግጭት ቀጠና እንዲሆን እና ሰብአዊ እርዳታ እንዳያልፍ አድርጓል ሲልም ገልጿል።

LEAVE A REPLY