ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኦሮሚያ ክልል ፣ ምስራቅ ወለጋ 5 ተማሪዎች እና አንድ በንግድ ስራ የሚተዳደር ግለሰብ በድምሩ 6 ሰዎች ታግተዋል።
የፌደራል የደኅንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል እገታውን ሸኔ እንደፈፀመ ገልፆ የታገቱትን ግለሰቦች ለማስለቀቅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አሳውቋል።
ግብረብረ ኃይሉ ታጋቾቹ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ ሲጓዙ ምስራቅ ወለጋ ጎቡ ሰዮ ወረዳ ልዩ ስሙ ባፋኖ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ነው ጥር 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰአት አካባቢ በሸኔ ታፍነው የተወሰዱት ብሏል።
ግብረ ኃይሉ ታጋቾችን የማስለቀቁ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑንና እርምጃዎችን ተከትሎ የሚገኘውን ውጤት በቀጣይ ለህዝቡ እንደሚያሳወቅ ገልጿል።