ጠ/ሚ/ትር አብይ አህመድ በድርቅ ለተጎዱ ቦታዎች ለመጎብኘት ጅጅጋ ገቡ

ጠ/ሚ/ትር አብይ አህመድ በድርቅ ለተጎዱ ቦታዎች ለመጎብኘት ጅጅጋ ገቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጅግጅጋ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል ቀብሪበያን ጎበኙ በጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ የተመራ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ከክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን ዛሬ ማለዳ ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “በጊዜያዊነት የውኃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን፣ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን አቅርቦት እናሳድጋለን” ሲሉ አስታውቀዋል።

ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉም አክለዋል።

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ230 ሺህ በላይ እንስሳት ሲሞቱ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ከክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

LEAVE A REPLY