ለትግራይ ህዝብ እርዳታ ሊያደርሱ ሲጓዙ የነበሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደኃላ ተመልሰዋል ተባለ

ለትግራይ ህዝብ እርዳታ ሊያደርሱ ሲጓዙ የነበሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደኃላ ተመልሰዋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህወሓት ቡድን የተለያዩ መሰረታዊ የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ዘልቀው እንዳይገቡ አፋር ክልል አብአላ ውስጥ ታግደው ተይዘዋል ብሏል።

በሌላ በኩል እረዳታ አደረሰው እየተመለሱ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ እንዲመለሱ መገደዳቸው ተገለፀ

የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው “ከሰመራ ታጅበው ወደ ትግራይ ሊገቡ ነበር” ተብሎ የተነገሯቸው 27 የጭነት መኪኖች ወደ መቀሌ እንዳይገቡ ተደርገዋል ብለዋል።

በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህመሃት ቡድን በአፋር ክልል በአዲስ መልክ ጥቃት እየፈጸመ በመሆኑ ሰብዓዊ አቅርቦትን ትግራይ ክልል አድርሰው ሲመለሱ የነበሩ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች እንዳይወጡ መታገዳቸው ተገልጿል።

ቡድኑ ተሽከርካሪዎቹን ከግማሽ መንገድ በኋላ ወደ መቀሌ እንዲመለሱ ማስገደዱን በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ቡድኑ በአፋር እንደ አዲስ በጀመረው ወረራና ጭፍጨፋ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች መፈናቀላቸውንም የጽሕፈት ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
የህወሃት ቡድን መሪዎች ሕዝቡን በማስራብ ለፖለቲካ አጀንዳቸው በግልጽ ሲጠቀሙበት እየተስተዋለ መሆኑንም መረጃው ጠቁሟል፡፡

ቡድኑ ከዚህ ቀደምም ሰብዓዊ አቅርቦትን ጭነው ወደ ትግራይ የገቡ 1 ሺህ 10 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች እርዳታውን አራግፈው እንዳይመለሱ በማድረግ፣ ለታጣቂዎቹና ከአማራና አፋር ለዘረፋቸው ንብረቶች ማመላለሻነት ሲጠቀም መቆየቱ ይታወሳል።

በዚህ ሂደት ግን የተሽከርካሪዎቹ ባለቤት የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራምም ይሁን ሰብዓዊነት ያሳስበናል በሚል ኢትዮጵያ ላይ የዘመቱ መንግሥታትና ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ድምፃቸውን አጥፍተዋል ተብሏል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ህወሓት የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በሌለበት በአፋር ክልል አብአላ ላይ በከፍተው ጥቃት እያደረሰ ነው ብሏል ለትግራይ ህዝብ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ሊገቡ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደኃላ ለመመለስ ተገደዋል ብሏል።

ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ሲል በትዊተር ገፃቸው ላይ የጻፉት የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው “ከሰመራ ታጅበው ወደ ትግራይ ሊገቡ ነበር” ተብሎ የተነገሯቸው ሰብአዊ ዕርዳታ የጫኑ የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም 27 የጭነት መኪኖች ወደ መቀሌ እንዳይገቡ ተደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY