የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጸደቀ

PM Netanyahu addressing the Ethiopian parliament

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ሎሚ በዶ ኮሚቴው ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጥያቄ ማፅደቁን አስታውቀዋል፡፡

ረቂቅ በጀቱ የተቋረጡ እና በጅምር ላይ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ከማስቀጠል በተጨማሪ በኮሮና ቫይርስ እና በጦርነቱ ምክንያት የወጡ ወጪዎችን ለመሸፈን እንደሚውል ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የማሕበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ረቂቅ አዋጅንም አጽድቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ህክምና ማግኘት ለማይችሉ የሕብረሰተብ ክፍሎች ፍትሃዊ፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የጤና ሽፋን በመስጠት እንዲታከሙ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ምክትል አፈጉባኤዋ ተናግረዋል፡፡

የአማካሪ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው አጀንዳዎቹ፣ ተገቢ እና የሕዝቡን ችግር ለመፍታት ሚናቸው የጎላ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

LEAVE A REPLY