የአፍሪካን የሰላም እና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል ሲሉ...

የአፍሪካን የሰላም እና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል ሲሉ ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአፍሪካ በየአቅጣጫው እያጋጠመ ያለውና የተለያየ ቅርፅ የያዘውን የሰላም እና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ተናገሩ፡፡

40ኛው የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የአፍሪካ አህጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በስብሰባው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ተፅዕኖ እና ለመቋቋም እየተደረገ ስላለው ጥረት፣ የአጀንዳ 2063 የአፈጻጸም ሂደት፣ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አተገባበር እንቅስቃሴ እና መሰል ወቅታዊ የአህጉሪቷን አጀንዳዎች ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

LEAVE A REPLY