ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሀመድ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው በቀብሪ በያህ ወረዳ መረጋቾ ቀበሌ የሚገኙ ዜጎችን ጎብኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እና ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኘበትን ሁኔታ የተመለከቱት በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በቀብሪ በያህ ወረዳ መረጋቾ ቀበሌ የሚገኙ ዜጎችን ነው የጎበኙት።
ፕሬዚዳንቷ እና ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በድርቁ የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኙበትን ሁኔታ የተመለከቱት ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድን ጨምሮ ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል።