ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄዱና የሰነድ ማሻሻያ ያላደረጉ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጉባኤያቸውን በማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንድታስገቡ ሲል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 23 ቀን 2014 ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር መሠረት ከ6ተኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱና የሰነድ ማሻሻያ እንዲያደርጉ የተገለፀላቸው ብሏል ቦርዱ።
ፓርቲዎቹ የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ በምክክሩ ወቅትም ለፓርቲዎች መገለጹን በማስታወስ።
በዚህም መሰረት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ ገዥዉን ፓርቲ ጨምሮ 13 የ ፌደራልና 13 የክልል ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ ቦርዱ በዛሬዉ እለት አሳስቧል።