ዓለም ባንክ ለሶማሌ ክልል ከ64 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ መደበ

ዓለም ባንክ ለሶማሌ ክልል ከ64 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ መደበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ከክልሉ ርዕስ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባለው ሁኔታና ለድርቁ እየተሰጠ ባለው ምላሽ ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸዉም ተሰመቷል።

የሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ምክኒያት በርካቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለጉዳት ተዳርገዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ እንስሳት በድርቁ ምክኒያት እየሞቱ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ከምክክሩ በኋላ ዓለም ባንክ በሶማሌ ክልል ለተከሰተው ድርቅ አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ 64 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ገልፀዋል።

ከተመደበው ድጋፍ ውስጥ 38 ሚሊዮን ዶላሩ አሁን የሚሰጥ መሆኑን የታወቀ ሲሆን የዓለም ባንክ በዚህ ወሳኝ ጊዜ ድጋፉን በማድረጉም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY